መተዳደሪያ ደንብ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኦታዋ ደብረ ጽዮን ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ
የኦታዋ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን የራስዋ የሆነ የመተዳደሪያ ደንብ ያላትና በካናዳ አትራፊ ያልሆኑ የበጎ-አድራጎት ድርጅቶች በሚተዳደሩበት ሕግ መሰረት እንዲደነገግ እና እንዲሠራበት አባላቱን በሙሉ አወያይታ ያዘጋጀችው ደንብ ነው፡፡ የመተዳደሪያ ደንቡ የቤተከርስቲያኗን ትምህርት እና ቀኖና፡ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎቸ ያጣጣመመ ነው።
ሰለዚህ በመተዳደሪያ ደንብ አማካይነት የተሠራችው ቤተ-ክርስቲያን፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለአንዳች የኢኮኖሚ ጥቅም ሆነ የፖለቲካ ፍላጎት አገልጋይ አትሆንም። ቤተ-ክርስቲያኗ አትራፊ ድርጅት አይደለችም፤ የእምነት ተቁኣም እንጂ። መተዳደሪያ ደንቡ የአገልጋዮች፤ የምእመናንና መላው ወደ ቤተክርስቲያናችን የሚመጡትን ህዝበ ክርስቲያንን በሙሉ የሚያስተዳድር ነው። ከሰብካ ጉባኤ አወቃቀር እስከ አባላት ሃላፊነትና ግዴታ ድረስ ሁሉንም አካቶ የያዘ ስለሆነ ሁላችን በዚህ እንተዳደር ዘንድ ቤተክርስቲያን ከ 2006 ዓ/ም ጀምሮ ያዘጋጀችው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ሰኔ 2020