ያለፉ ትእይንቶች
የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ (በማቴ 16፡18)“በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም በሮች ደጆችም አይበረቱባትን፤አይችሏትም” በማለት ቤተክርስቲያን ማለትም ክርስቲያንነትን በሰው ልጅ ላይ እንደሚሰራ ዓለት እንደሆነ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስምዖን በራሱ ባለው በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)
የላይኛውን እንደ መግቢያ ካየነው፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ደሞ እለት ከእለት ከሚደረገው ሥርአተ-ቤተክርስቲያን ጎን ለጎን እንደ ጌታችን ቃል መሰረትበምእመኑ ላይ ዓለት ለመስራት ስትል ቤተክርስቲያን የምታካሂዳቸውና ከዚህ በፊት ያካናወነቻቸው ብዙ መንፈሳዊ ክንውኖች አሉ። ላልፉት አምስት አመታት እንኩዋን በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባኤዎች፤ የፍቅር ማእዶች (አጋፔ)፤ ትእይንተ-ክንውኖችና የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ሲደረጉ ከቆዩት መካከል ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህ ክንውኖች ለምእመኑ በሚሰጡበት ጊዜ የሚያስገትን ጥቅሞች እንደሚከተለው በጥቂቱ ማየት ይቻላል። በፎቶ ማሳያው ያለውንም በመመልከት ስላለፉት አበይት ክንውኖች የበለጠ መረዳት ይችላሉ።
በደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ካገለገሉ የሃገራችን ሰባክያነ ወንጌል እና ዘማርያን መካከል እነዚህ ይገኙበታል፡፡
- መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ (ከኢትዮጵያ)፤
- ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ (ከኢትዮጵያ)፤
- ሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (ከኢትዮጵያ)፤
- ዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኽኝ (ከኢትዮጵያ)፤
- መምህር ዘላለም ወንድሙ (ከኢትዮጵያ)፤
- መምህር ምህረተዓብ አሰፋ (ከኢትዮጵያ)፤
- መላከሳሌም ቆሞስ አባ ገብረኪዳን (ከላስቭጋስ)፤
- ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው (ዴንቨር)፤
- ዲ/ን ጎርጎሪዮስ ደጀኔ (ከዴንቨር)፤
- በኩረመዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ (ከኢትዮጵያ)፤
- ሊቀመዘምራን ይልማ ሃይሉ (ከሚኒያፖሊስ)፤
- ቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ በሃኑ (ከኢትዮጵያ)፤
- ዘማሪት እግዚሃርያ ይልማ (ከሚኒያፖሊስ)፤
- ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ (ከኢትዮጵያ)
ለአገልግሎታቸው በቤተክርስቲያናችን ስም እግዚአብሄር ይስጥልን፤ ቃለ ህይወት ያሰማልን እንላለን፡፡