ለደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወርሃዊ አስተዋጽኦ ለምታደርጉ ምእመናን በሙሉ፦
በነገው እለት ለቤተክርስቲያኗ ሁሌ በየወሩ የምትከፍሉትን ወርሃዊ አስተዋጾ ከባንካችሁ ወጪ የሚደረግበት ቀን ነው፡፡
በአለማችን ላይ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከስራ በመገለል ምክንያት ወርሃዊ የቤተክርስቲያን አስተዋጾ መክፈል የሚከብደው ሰው ካለ ወጪ ከማድረጋችን በፊት እስከነገ ማታ ስልክ በመደወል ታሳውቁን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን፡፡
ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ብዙ ወጪዎች ቢኖርባትም ቤተክርስትያናችን ከእግዚሃር ቀጥሎ እናንተ ስትኖሩ ስለሆነ የምትኖረው ለተወሰነ ጊዜ ክፍያ ይቀነስልን ወይንም ክፍያውን አቁሙልን የምትሉ አባላት ካላችሁ እስከ አፕሪል 23/2020 ማታ ድርስ ለወንድም ዘራዓይ ፡ ለእህታችን በርኸ ወይንም ለወንድም ቶማስ አንድታሳውቁልን በትህትና እናሳስባለን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር!
የደብሩ የሰበካ ጉባኤ